የንግድ ስራ ፍቃድ እድሳት - ለግለሰብ ነጋዴ

ለግለሰብ ነጋዴ

አመልካቹ  የአዲስ የንግድ ፈቃድ የማመልከቻ ቅጹን በመሙላት ከሚከተሉት ሰነዶች ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለበት፡-

 1. ማመልከቻዉ በውክልና ወይም በሞግዚት ከሆነ የውክልና ወይም የሞግዚትነት ህጋዊ ሰነድ
 2. አዲስ የተሰጠ ወይም የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
 3. የአመልካቹ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የተነሳው ፓስፖርት መጠን ያለዉ 2 ጉርድ ፎቶግራፍ 
 4. የውጭ ባለሀብት ከሆነ የኢንቨስትመንትና የፀና የመኖሪያ ፈቃዱን፣
 5. እንደ ሀገር ውስጥ ባለሀብት የተቆጠረ የውጭ ሀገር ዜጋ ከሆነ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ የተሰጠ ማረጋገጫና የመኖሪያ ፈቃድ፣
 6. ማመልከቻው የቀረበው በወኪል ከሆነ የተረጋገጠ የውክልና ሠነድ እና የተወካዩ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ፣
 7. ለንግድ ሥራው የተመደበውን ካፒታል የሚያሳይ ማስረጃ፣ እና
 8. ግድ ሥራው የሚከናወንበት ቤት ለንግድ ሥራው ተስማሚ መሆኑን ከሚመለከተው የመንግሥት መስሪያ ቤት የተሰጠ ማረጋገጫ፣ አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡የዋና መሥሪያ ቤቱ  እና ያለም ከሆነ የቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶቹን ትክክለኛ አድራሻ፣ እና ለንግድ ሥራ የሚጠቀምበት ቤት የራሱ ከሆነ የባለ ይዞታነት ካርታ፣ የኪራይ ከሆነ በሰነድ አረጋጋጭ የተረጋገጠ  ሰነድ እና ስለቤቱ አድራሻ ከቀበሌ መስተዳድር የሚሰጥ ማረጋገጫ፡
 9. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
 10. ሥራዉ ከሚመለከተዉ መስሪያ ቤት የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊቀርብባቸው የሚገቡ የንግድ ሥራዎችን አስመልክቶ ማረጋገጫ የሚሰጡ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች አግባብ ያለው ባለሥልጣንን ፈቃድ ከመስጠቱ በፊት ማረጋገጫ እንዲጠይቅ ሊያሳስቡ ይችላሉ፡፡

ለአዲስ የንግድ ፈቃድ ለማከናወን ባለሙያዉ የሚፈፅማቸዉ

 1. አዲስ የንግድ ስራ ፈቃድ የማመልከቻ ቅጽ  መስጠት እና አሞላሉን ማስረዳት
 2. አዲስ የንግድ ፈቃድ ማመልከቻ ተቀብሎ ቅፁ በትክክል መሞላቱንና ሰነዶች መሟላታቸውን  ማረጋገጥ
 3. አዲስ የንግድ ፈቃድ አገልግሎት ክፍያ ማስፈፀም
 4. ልዩ ተጣቃሽ የምዝገባ ቁጥሩን እና አዲስ የፈቃድ ቁጥር በመስጠት ፈቃዱን ማዘጋጀት
 5. የተዘጋጀውን አዲስ የንግድ ስራ ፈቃድ በፊርማ በማረጋገጥ እና ቲተሩን በማተም ማስተላለፍ
 6. አዲስ የንግድ ስራ ፈቃድ መረጃውን ወደ ዳታ ቤዝ ማስገባት
 7. የተዘጋጀውን አዲስ የንግድ ስራ ፈቃድ መዝግቦ ፎቶግራፍ በመለጠፍ ማህተም አድርጎ ለባለጉዳዩ ማስረከብ