News News

ኢትዮጵያ በመሰረተ ልማት እያሳየች ያለው ለውጥ መልካም እንደሆነ ተገለጸ

ነሐሴ 18 ቀን 2010ዓ.ም

ኢትዮጵያ በመሰረተ ልማት እያሳየች ያለው ለውጥ መልካም እንደሆነ ተገለጸ 

 የኢፌዴሪ ንግድ ሚኒስቴር ክቡር አቶ መላኩ አለበል  የቬትናም ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከክቡር ትራን ትዋን አን እና  የልዑካን ቡድኑን  በጽህፈት ቤታቸው  አዳራሻቸው ተቀብለው አነጋገሩ ፡፡

በውይይታቸው ላይ ክቡር አቶ መላኩ አለበል ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የምትልካቸው ምርቶች የግብርና ውጤቶች በመሆኑ የቬትናም ባለሃብቶች በግብርና ምርት ላይ እሴት በመጨመር ፣በማዕድን እና በመሰረተ ልማት ቢሰማሩ ውጤታማ እንደሚሆኑ አባራርተውላቸዋል ፡፡

እንዲሁም የቬትናሙ የንግድና የኢዱስትሪ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት በቴሌ ኮም ፣በሃይል አቅርቦት እና በአጠቃላይ በመሰረተ ልማት እያሳየችው ያለው ዕድገት አመርቂ እንደሆነ ገልጸው በአገራቸው በኩል ተባብረው እንደሚስሩ ቃል ገብተዋል ፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያ የንግድ ልዑክ ቬትናምን እንዲጎበኙ ግብዣ አቅርበውላቸዋል፡፡

በመጨረሻም የቬትንም የንግድ ሉዑካኑ ስጦታ ለክቡር ሚኒስትሩ አበርክተውላቸዋል ፡፡