News News

ኢትዮጵያና ቱርክ ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ተነገረ

ህዳር 20/2011 ዓ.ም

ኢትዮጵያና ቱርክ ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ተነገረ

    የቀድሞ የቱርክ አምባሳደር ፋቲህ ዑሉሰይ በኢትዮጵያ የሦስት አመት የስራ ቆይታ ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ ሀገራቸው መሰናበታቸውን ተከትሎ ህዳር 19/2011 ዓ.ም ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒሰትሯ ክብርት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ጋር ውይይት አካሔዱ፡፡

በውይይት ወቅት አምባሳደሩ እንደተናገሩት “በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ፈጣንየማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት፣ ኢንቨስትንመንትና የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር መንግስታቸው በትኩረት ይሰራል፡፡” በዚህ ረገድ በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ከ150 በላይ የቱርክ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ በጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሯ ክብርት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔርም በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የረጅም ጊዜ የንግድና ኢንቨስትመንት ታሪካዊ ግንኙነት ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ መንግስታቸውን የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ አያዘውም ክብርት ሚኒስትሯ መንግስት ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ዘርፍ የተለየ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን በዚህ ሂደት ዕሴት እየተጨመረባቸው የሚመረቱ የኤክስፖርት ምርቶች ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ከፍተኛ ድርሻ ይኖራቸዋል ብሏል፡፡ በዚህ ረገድ የቱርክ ባለሃብቶች እያደሩጉት ያለው ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ለዜጎች የስራ ዕድል ፈጠራ እና ለወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ መንግስት የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግም ለተሰናባቹ አምባሳደር ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ክብርት ሚኒስትሯ ለተሰናባቹ አምባሳደር የኢትዮጵያን ቡና ስጦታ በማበርከት ውይይታቸውን ቋጭተዋል፡፡

 

         የንግድና ኢንዱስተሪ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ከሙኒኬሸን ጉዳዮች ጽ/ቤት