News News

ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ በፀሐይ ኃይል የሚሰሩ ምርቶች የጥራት ቁጥጥር አሰራር ሊሻሻል ነው

ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ በፀሐይ ኃይል የሚሰሩ ምርቶች የጥራት ቁጥጥር አሰራር ሊሻሻል ነው

ከዚህ በፊት ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው በፀሐይ ኃይል የሚሰሩ (የሶላር ምርቶች) ላይ የሚደረገው የጥራት ቁጥጥር አሰራር በአስመጪዎች በኩል ቅሬታ በመፍጠሩ አሰራሩን ሊያሻሽል እንደሆነ የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት (መስከረም 4 ቀን 2011 ዓ.ም) በፀሐይ ኃይል የሚሰሩ ምርቶች አስመጪዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በሐርመኒ ሆቴል ውይይት አካሂዷል፡፡

በንግድ ሚኒስቴር የንግድ አሰራርና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ ውይይቱን በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት ከሶላር ምርቶች የቁጥጥር አሰራር ጋር በተያያዘ በናሙና አወሳሰድ፣ በላብራቶሪ ክፍያ እና የኢንቮይስ (ምርቱ የተገዛበት ዋጋ) 0.5% በባንክ በመያዣነት ማስቀመጥ ጋር ተያይዞ ያለውን አሰራር ማስተካከያ እንዲደረግ ላለፉት ሁለት ዓመታት ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቅሬታዎች ቀርበዋል፡፡

ይህንን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዲሱ አመራር ጉዳዩን በጥልቀት ተመልክቶት የመጨረሻ እልባት መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ በዘርፉ ውስጥ ያሉ ባለድርሻ አካላት፣ የንግዱ ማህበረሰብ እና ሸማቹ ህብረተሰብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የንግድ ሚኒስቴር ከ15 ዋት በታች የሆኑ በታዳሽ ኃይል የሚሰሩ ምርቶች አስገዳጅ ደረጃ ውስጥ ተካተው ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ የጥራት ቁጥጥር ሲያደረግ ቆይቷል፡፡ የጥራት ቁጥጥሩ ከደረጃ በታች (ጥራታቸውን ያልጠበቁ) ምርቶች ወደ ገበያ እንዳይገቡ በማድረግ የሸማቾችን ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ናሙና ተወስዶ ወደ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ላብራቶሪ የሚላክበትና አስመጪዎች ምርቱ የገዙበት ዋጋ 0.5% ለዋስትና የሚያሱዝበትና ያስገቡት ምርት ከደረጃ በታች ከሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ የሚሆንበት ጊዜያዊ አሰራር ተዘርግቶ ለሁለት ዓመታት ሲሰራበት ቆይቷል፡፡

ይሁንና የሶላር ምርቶቹ በሀገር ውስጥ ያለው የላብራቶሪ አቅም ውስንነትና ፍተሻው በባህሪው ረጅም ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ እስከ አሁን ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው አሰራር የአስመጪዎች ንብረት በጉምሩክ መጋዘን መከማቸት፣ ላልተፈለገ የመጋዘን ኪራይ፣ የጊዜ ብክነት እና ዕቃው በጊዜ ስራ ላይ ባለመዋሉ ባትሪው ከአገልግሎት ውጪ መሆኑና መድከም እንዲሁም በወደብ ውስጥ የቦታ ጥበት በመፍጠር ደንበኞች ቅሬታ እንዲያነሱ አድርጓል፡፡

በንግድ ሚኒስቴር የገቢና ወጪ ዕቃዎች ጥራት ቁጥጥር ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ኢያሱ ስምኦን በበኩላቸው ከሶላር ምርቶች የጥራት ቁጥጥር አሰራር ጋር ተያይዞ የተከሰተውን ችግር ለመቅረፍ የንግድ ሚኒስቴር የአጭርና የረጅም ጊዜ መፍትሄ እንዳቀረበ አብራርተዋል፡፡ እንደ አቶ ኢያሱ ገለፃ በአጭር ጊዜ መፍትሄ በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የተወሰዱ ናሙናዎች ሙሉ የፍተሻ ውጤት እንዲቀርብ በአጭር ጊዜ ገደብ ለባለንብረቶች እንዲገለፅ ማድረግ፣ በሚመጣው ውጤት መሰረት ሙሉ ፍተሸ ተደርጎ አስገዳጅ የደረጃውን መስፈርት ላሟሉ ባለንብረቶች ለዋስትና የተያዘባቸው ገንዘብ በአስቸኳይ እንዲመለስላቸው ማድረግ እና አስመጪዎች ለሶላር ምርት የሚያቀርቡትን ሰርተፍኬት ይዘት ተጠያቂነት ባለው አግባብ አለም አቀፍ ዕውቅና ካለው ድርጅት እንዲያቀርቡ በማድረግ ለብሔራዊ ባንክ በደብዳቤ በማሳወቅ ዕቃውን ከመጫን በፊት ሲያስፈቅዱ ማቅረብ ያለባቸውን ሰርተፍኬት አውቀው እንዲያመጡ እገዛ ማድረግ የሚሉ አማራጮች ቀርበዋል፡፡

በረጅም ጊዜ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሶላር ምርትን ከሚፈትሹ አካላት ጋር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውል በመዋዋል አስገዳጅ ደረጃ ለወጣላቸው ምርቶች ብቻ በኢትዮጵያ ደረጃ መሰረት ተፈትሾ በዚህ አግባብ ሰርተፍኬት የሚቀርብበትን አሰራር መዘርጋት እና የሀገር ውስጥ የመፈተሽ አቅምን በማጎልበት በሰርተፍኬት የገቡ ምርቶችን ከገበያ ናሙና በመውሰድ ላብራቶሪ በማስፈተሽ የቼክና ባላንስ ስራ መስራትና ጥራትን ባላሟላ ምርት አስመጪውና ሰርትፍኬት በሰጠው አካል ላይ እርምጃ መውሰድ እንደ መፍትሄ ተቀምጠዋል፡፡

የተሻሻላ በፀሐይ ኃይል የሚሰሩ ምርቶች የጥርት ቁጥጥር አሰራር ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

የኢፌዲሪ ንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትNo comments yet. Be the first.

News Archive News Archive

— 10 Items per Page
Showing 1 - 10 of 39 results.