News News

ከቆዳና ሌጦ ግብይት ተዋንያንና ከአምራቾች ጋር በዘርፉ በሚታዩ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደ፡፡

 

ጥቅምት 27 2012 (ንኢሚ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከቆዳና ሌጦ ግብይት ተዋንያንና ከአምራቾች ጋር በዘርፉ በሚታዩ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደ፡፡

በውይይቱ ተሳታፊዎች ከተነሱት የቆዳና ሌጦ ኢንዱስትሪ ሴክተር ተግዳሮቶች መካከል በጥሬ ቆዳና ሌጦ አቅራቢዎች፣ አዘጋጆችና አምራች ኢንዱስትሪዎች መካከል ያለው የገበያ ትስስር ደካማ በመሆኑ ምክንያት ጥሬ ቆዳና ሌጦ ለብክነት መዳረግና የጥሬ ቆዳና ሌጦ ጥራትን ለማስጠበቅና ለማቆየት የሚረዱ ግብዓቶች እጥረት መኖር ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የጥሬ ቆዳና ሌጦ አቅራቢዎች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ብርሃኑ አባተ መንግስት ከዘርፉ ተዋንያን ጋር በተመባበር በጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የማሻሻያ እርምጃዎችን ቢወስድ በዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃት ይፈጠራል ብለዋል፡፡

በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የጨርቃጨርቅና ቆዳ አግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረየስ በአጠቃላይ የአምራች ኢንዱስትሪውን በተለይ ደግሞ የቆዳና ሌጦ ግብይትን በማሻሻል ቆዳና የቆዳ ምርቶች አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ አምራቾችና አቅራቢ ነጋዴዎች ተቀናጅው በመስራት የግብዓት አቅርቦትና ፍላጎት እንዲጣጣምና ዘርፉ እንዲነቃቃ በማድረግ ረገድ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ በአንክሮ አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም መንግስት የዘርፉን ተግዳሮች በማስወገድ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አማካኝነት ለፖሊሲ ማሻሻያዎች ግብዓት የሚሆኑ የጥናት ውጤቶችን ጨምሮ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው በቅርቡ የዘርፉ ተዋናዮች፣ የባለድርሻ ተቋማት ተወካዮችንና ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን አካላት ያካተተ ሀገር አቀፍ ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

 No comments yet. Be the first.

News Archive News Archive

— 10 Items per Page
Showing 1 - 10 of 45 results.