News News

#የግል ኩባንያዎች የሴት ሠራተኞችን ደህንነት እና መብት የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸው ተገለጸ

 የግል ኩባንያዎች የሴት ሰራተኞቻቸውን ደህንነትና መብት የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸው ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የባለድርሻ አካላት ጋር ምቹ የሥራ አካባቢ በመፍጠር እና በስራ ላይ በሚደርሱ ጉዳቶች ዙሪያ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ውይይት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ በተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት የፖሊሲ ስፔሻሊስት አቶ ነብዩ መርሻ እንደተናገሩት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ተቀጥረው የሚገኙ ሴት እህቶቻችን በርካታ ችግሮች እየገጠማቸው ነው፡፡ በቂ ደመወዝ አለመከፈል፣ጉልበት ተኮር ስራዎች ላይ ብቻ እንዲሳተፉ ማድረግ እንዲሁም በሚሰሩባቸው ተቋማት ላይ ጻታን መሠረት ያደረጉ ህክምና አለማግኘት የተስተዋሉ ችግሮች ሲሆኑ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ በተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት በቀጣይ መጠነ ሰፊ ስራዎችን ለመስራት ዕቅድ ተይዟል፡፡

በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሴቶች፣ወጣቶችና ህጻናት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ዳምጤ በበኩላቸው መንግስት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪውን ለማዘመን በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል ያሉ ሲሆን ይህም ግቡን የሚመታው የኩባንያ ባለቤቶች ትርፍ ከማግኘት በዘለለ በድርጅታቸው ተቀጥረው ለሚሰሩ ሴቶች የስራ ላይ ደህንነት እና ጥቅማ ጥቅም ያለ አንዳች መሸራረፍ ሲረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡

ማኒፋክቸሪንግ ኩባንያዎች ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥተው መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው የተናገሩት ዳይሬክተሯ ሚኒስቴር መ/ቤቱም የሴቶች የስራ ላይ ደህንነት ብሎም ጥቅማ ጥቅም እንዲረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቀጣይ በርካታ ስራዎችን ለመስራት ዕቅድ አለውም ብለዋል ፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የማኑፋክቸሪንግ ባለቤቶችን ጨምሮ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ እና ከተጠሪ ተቋማት የተውጣጡ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡No comments yet. Be the first.

News Archive News Archive

— 10 Items per Page
Showing 1 - 10 of 45 results.