News News

ቆዳ ፋብሪካዎች አጠቃላይ ከሚያመርቱት የቆዳ ምርት 30 በመቶ የሚሆነውን ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ቆዳ ፋብሪካዎች አጠቃላይ ከሚያመርቱት የቆዳ ምርት 30 በመቶ የሚሆነውን ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
 


በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ በቆዳ ኢንዲስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና በአስራ ሶስት የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት በዌት ብሉና ፒክል ምርቶች ላይ ተጥሎ የነበረው 50 በመቶ ታክስ ሙሉ በሙሉ መነሳቱ ተከትሎ የቆዳ ጫማ ፣የቆዳ አልባሳትና ሌሎች የቆዳ ውጤቶች ምርት በማምረት ሥራ ላይ የተሠማሩ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት የሚጠቀሙበት የተጠናቀቀ ቆዳ አቅርቦት ችግር እንዳይገጥማቸው ለማድረግ እና በአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተገነባው የቆዳ ማጠናቀቅ አቅም እየተሸረሸረ እንዳይሄድ ቆዳ ፋብሪካዎች አጠቃላይ ከሚያመርቱት የቆዳ ምርት ውስጥ በመጠን ቢያንስ 30 በመቶ የሚሆነውን ምርታቸውን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ጥር 05 2012 . ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን ከተፈራረሙት ውስጥ የቆዳ ኢንዲስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትን ጨምሮ አዲስአበባ ቆዳ አክሲዩን ማህበር ሆራ ቆዳ /የተ/የግ/ማህበር ሞጆ ቆዳ አክሲዮን ማህበር ኮልቦ የቆዳ ማልፊያና ማለስለሻ /የተ/የግ/ማህበር ባቱ የቆዳ ማልፊያ /የተ/የግ/ማህበር ዴቭኢምፔክስ ኢንተርፕራይዝ ባህርዳር ቆዳ ፋብሪካ /የተ/የግ/ማህበር ሼባ ሌዘር ኢንዱስትሪ /የተ/የግ/ማህበር ኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ /የተ/የግ/ማህበር ድሬ ኢንዱስትሪዎች /የተ/የግ/ማህበር ገላን ቆዳ /የተ/የግ/ማህበር ሐፈደ /የተ/የግ/ማህበር ዋልያ ሌዘርና ሌዘር ፕሮዳክትስ /የተ/የግ/ማህበር እና ይልማ እሸቴ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ፋብሪካ ይገኙበታል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ ከጥር 5 2012. ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡No comments yet. Be the first.

News Archive News Archive

— 10 Items per Page
Showing 1 - 10 of 48 results.