News

News and updates News and updates

ቆዳ ፋብሪካዎች አጠቃላይ ከሚያመርቱት የቆዳ ምርት 30 በመቶ የሚሆነውን ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ በቆዳ ኢንዲስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና በአስራ ሶስት የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት በዌት ብሉና ፒክል ምርቶች ላይ ተጥሎ የነበረው 50 በመቶ ታክስ ሙሉ በሙሉ መነሳቱ ተከትሎ የቆዳ ጫማ ፣የቆዳ አልባሳትና ሌሎች የቆዳ ውጤቶች ምርት በማምረት ሥራ ላይ የተሠማሩ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት የሚጠቀሙበት የተጠናቀቀ ቆዳ አቅርቦት ችግር እንዳይገጥማቸው ለማድረግ እና በአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተገነባው የቆዳ ማጠናቀቅ አቅም እየተሸረሸረ እንዳይሄድ ቆዳ ፋብሪካዎች አጠቃላይ ከሚያመርቱት የቆዳ ምርት ውስጥ በመጠን ቢያንስ 30 በመቶ የሚሆነውን ምርታቸውን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ጥር 05፣ 2012 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡

የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ተግባር በመላ አገሪቱ ወጥ የሆነ፣ ቀልጣፋ ደረጃውን የጠበቀ አሰራር ሥርዓት መኖሩ አስተዋጽኦው ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በውክልና ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተሰጡ የመመስረቻ ጽሁፍ መተዳደሪያ ደንብ እና ማሻሻያዎች ላይ ጥር 6 ቀን 2012 ዓ.ም ስልጠና በተሰጠበት ወቅት በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ አሰራርና ሪጉላቶሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ግዛው ተክሌ እንደተናገሩት በሰነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ ተቋማት መካከል ግልጽ ግንኙነት የሚፈጥር እና ያለአግባብ የሚረጋገጡ ሰነዶችን መቆጣጠር በሰዎች መካከል የሚደረጉ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ግንኙነቶችን በማቀላጠፍ ከፍተኛ ሚና ስለሚኖረው ሚኒስቴር መስራቤቱ ይህን ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡

ኢንዱትሪ ሚኒስቴር ፣ በቆዳ ኢንዲስትሪ ልማት ኢንስቲዩት እና በአስራ ሶስት የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡

በንግድና ኢንዱትሪ ሚኒስቴር፣ በቆዳ ኢንዲስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና በአስራ ሶስት የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ዋና ዓላማ ለውጭ ገበያ በሚቀርበው ጥሬ እና በከፊል የተዘጋጀ ቆዳና ሌጦ ላይ የሚከፈል ታክስ እንደገና ለማሻሻል በወጣ መመሪያ ቁጥር 61/2012 ቀደም ሲል በዌት ብሉና ፒክል ምርቶች ላይ ተጥሎ የነበረው 50 በመቶ ታክስ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ ተደርጓል፡፡

e-Services e-Services

eServices

Ministry of Trade App Ministry of Trade App

 

Meet the Minister Meet the Minister

Selected Forms Selected Forms

Back

Trade Name Verification

Download Resource