News

ታዋቂው ቤልጀማዊ ፎቶግራፈር የፎቶግራፍ መጽሀፍ /Photography Book/ ለቱሪዝም ሚኒስቴር አበረከተ

ኢትዮጵያን ከ20 አመታት በላይ ፎቶግራፍና ቪዲዮ የቀረጸው ታዋቂው ቤልጀማዊ ፎቶግራፈር Olivier Bourguet ያዘጋጀውን መጽሐፍ (Photography Book) እና ዶክመንታሪ ፊልም ለኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በስጦታ አበርክቷል። መጽሀፉ በፈረንሳይኛ ቋንቋ መግለጫ (Photography caption) የያዘ ነው። በዕለቱም የቤልጀም አምባሳደር H.E. Stefaan Thijs እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በቀጣይ መሰል የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ፎቶግራፈሮች

Read More »

አዳዲስ የቱሪዝም መስህቦችን ለማስተዋወቅ ያለመ የተራራ ላይ የብስክሌት ጉዞ ፕሮግራም ተካሄደ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከአንኮበር ወረዳ ጀምሮ አስከ አፋር ድረስ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ አላማው ያደረገ የእግር ጉዞ፣ፓራግላዲንግ እና የ16 ኪሎ ሜትር የተራራ ላይ የብስክሌት ጉዞ ተካሄደ። ፕሮግራሙን ያዘጋጁት በኢትዮጵያ “Ride the rift”በሚል ፕሮግራም ቱሪዝም ሚኒስቴር ከአራት ታዋቂ አስጎብኚ ድርጅቶች ከተስፋ ቱር፣ ዳይናስቲ ኢትዮጵያ ቱርስ፣ሰሜን ኢኮ ቱርስ እና ኢትዮ ሳይክሊንግ ሆሊደይስ ጋር በመሆን ነዉ፡፡

Read More »

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጃው ጂይዋን ጋር ተወያዩ

አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጃው ጂይዋን ጋር በኢትዮጵያ ቱሪዝምን ለማጠናከር እና ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት አድርገዋል። አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እንደገለጹት ጎብኚዎችን ከአለም አቀፍ ገበያ ለመሳብ ያለውን ጥረት እና የቻይና ቱሪስቶችን ለመቀበል ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል። የውይይቱ ዋና ዓላማ ሁለቱ ሀገራት በቱሪዝም ዘርፉ ላይ በጋራ ለመስራት ያለመ ነው ተብሏል።

Read More »

የ22ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር ተካሄደ

40 ሺህ ተሳታፊዎችን ያስተናገደው ይህ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ ታዋቂ የውጭና የሀገር ውስጥ አትሌቶች ተገኝተዋል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዓለም ከሚከናወኑ የጎዳና ላይ ታላላቅ ውድድሮች መካከል ከአፍሪካ በአንደኝነት በዓለም አቀፍ ደግሞ በስድስተኝነት የሚጠቅስ ሲሆን ከኢትዮጵያውያን ባሻገር የተለያዩ የውጭ ቱሪስቶች እና አትሌቶች በተወዳዳሪነት እየተሳተፉበትም ይገኛሉ።

Read More »

‘ICCA Skills’ በሚል ርዕስ በስካይ ላይት ሆቴል ሲሰጥ የቆየው የአምስት ቀናት ስልጠና ተጠናቀቀ።

‘ICCA Skills’ በሚል ርዕስ በስካይ ላይት ሆቴል ሲሰጥ የቆየው የአምስት ቀናት ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ። የስልጠናው ዓላማ በዓለም አቀፍ የኹነት ዝግጅት ሙያ የዘርፉ ባለሙያዎችን ብቁ የማድረግ እና አለም አቀፍ እውቅና እንዲኖራቸው ለማስቻል ያለመ ነው። ሰልጣኞቹ በተሰጠው ስልጠና ጥሩ የሆነ የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ልምድ የቀሰሙ ሲሆን በምላሹም የቢዝነስ ኩነት ዘርፉን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በስልጠናው ላይ

Read More »

ቱሪዝም ሚኒስቴር ዘንድሮ የሚካሄደውን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ውድድር የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ለዓለም ማስተዋወቂያ መድረክ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ የቱሪዝም ሚኒስቴር ገልጿል። እሁድ የሚካሄደው የ2015 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ ተሰጥቷል። የቱሪዝም ሚኒስቴር የገበያ ልማትና ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፦ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው አትሌቶች መፍለቂያ ናት ብለዋል።

Read More »